የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በተመለከተ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት የተሰጠ መግለጫ !!!

የወያኔን ሥርዓት ዕድሜ ለማራዘም የሚደረግ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም !!!!

የወያኔ ሥርዓት የራሱን ሕግ በመጣሰ በሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ተብዬ ካድሬዎች አንኳ ሳይፀድቅ አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ የሕዝብን ትግል አቅጣጫ ለማስቀየር ያለመና ምንም አይነት ሕጋዊ መሠረት የሌለው የወያኔን ሥርዓት ዕድሜ ለማራዘም የታሰበ አዋጅ በመሆኑ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብ ሕብረት በጥብቅ ይቃወማል፡፡ አሁን እየተነሱ ያሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝብም ይሁን የሌሎች የአገራችን ሕዝቦች ጥያቄ የሕልውናና የማንነት ጥያቄ ስለሆነ አሁን ያለው የፓለቲካ ፕሮግራም የሆነው ሕገ አራዊት በተባበረ ሕዝብ ሕብረት ተወግዶ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሕገመንግስትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲመሠረት ነው፡፡ ምክንያቱም የወያኔ ሥርዓት መነሻና መድረሻው ፀረ ሕዝብ በመሆኑ በተወሰነ መንገድ ጥገናው ለውጥ (incremental change ) በማደረግ ዕድሜውን ለማራዘም መሞከሩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ባለመቻሉ አሁን ደግሞ ለሕዝብ ሰላም የሚል አሰቸካይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ የራሱን ዕድሜና የሕዝቡን የመከራ ጊዜ ለማራዘም የተደረገ በመሆኑ መላው ሕዝባችን በዚሁ ሳትታለሉ ትግላችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጠሉ ደምኢሕሕ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
ድል ለሕዝባችን!!
ደምኢሕሕ