ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት ለመላው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ የተላለፈ አስቸኳይ መልዕክት

የተከበራቹ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ እንድምታወቀው ጨቋኙን እና አምባገነኑን የወያኔ ሥርዓት ከነ አካተው ለማስወገድ ዴሞክራሲና እኩልነት የሠፈነባት ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ መላው የሃገራችን ህዝብ ያላሰለሰና የህወት መስዕዋትን የጠየቀ ትግል በማድረግ ላይ እንደምገኝ ይታወቃል።

በተደጋጋሚ ባስተላለፍናቸው የትግል ጥሪዎች ለመግለፅ እንደሞከርነው ላለፉት 27 ዓመታት በወያኔ አፋኝና ጨቋኝ ሥርዓት እንደለሎች አከባቢዎችና ክልሎች የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብም አሰቃቂ እና በዓይነቱ ወደር የለሽ የሆነ በደልና ጭቆና ሠለባ መሆኑ የምይካድ ሀቅ ነው። 

በጥቂት የወያኔ ባለሥልጣናት በተደራጁ የወንበዴዎች ቡድኖች በኢንቨስትመንት ሥም የደሃው አርሶ አደር መሬት ወረራ ; የደን ጭፍጨፋ ; የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ እና ከፍተኛ የሆነ የሠብዓዊ መብት ረገጣና አፈና እየተካሄደ ይገኛል።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የ አከባቢው ህዝብ በወዛደርነት ተቀጥረው የዕለት ተዕለት ህወታቸውን ይገፉ የነበሩበት የቴፒ፣ የበበቃ፣ የውሽውሽ ፣ የሊሙ እና የጉመሮ የቡናና የሻይ ተክል ድርጅቶች በወያኔ ጀለዎች በቁጥጥር ስር ውሎ ዜጎች ለረሃብና ለእርዛት የተዳረጉት በዚሁ አምባገነን ሥርዓት ሆኖ ሣለ የአከባቢው ህዝብ ጉዳዩን በዝምታ እያየው መሆኑ የችግሩን አሳሳቢነትና ግዝፈት እንድጨምር አደርጎታል።

የተከበራቹ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ከጊዜ ወደጊዜ እየበረታና እየገነፈለ የመጣውን የሠፍውን ህዝብ ቁጣና እቢተኝነት ለመመከት ;ለመቀልበስ; ወያኔ ዛሬም የንፁሀንን ህይወት በመሣሪያ አፈሙዝ እየቀጠፈ ሃገሪቱ  ወደለየለት ቀውስ እንድትገባ እያደረገ ነው።

ይሁን እንጅ (ሊነጋ ሲል ይጨልማልና) ይህንን አንባገነን ሥርዓት ግብዓተ መሬቱን ለማፋጠን መላው የሃገራችን ህዝብ እያደረገ ያለው መራርና ቁርጠኛ ትግል እየትፋፋመ በመሄድ ላይ ይገኛል።

ስለሆነም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ እየደረሰበት ካለው ዘርፈ ብዙ ጭቆናና የግፍ አገዛዝ ወቅቱ የሚጠይቀውን ማናቸውንም መዕሥዋትነት በመክፈል የትግል አጋርነቱን ያለ ማመንታት ሊያሳይ እንደሚገባ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ ህብረት እንደ ወትሮው ሁሉ ጥሪውን ያቀርባል።

በመጨረሻም የወያኔን የግፍ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመግርሰስ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በየቀኑ ህወታቸውን እየገበሩ ያሉ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ታላቅ አክብሮትና አድናቆት እየገለፅን የወያኔ መንግሥት እድሜውን ለማራዘም የሚያደርጋቸው ተስፋ አስቆራጭ በሚመስሉ የማደናገሪያና የማታለያ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ መላው ህዝብ ሣይዘናጋ ትግሉ በጀመረው ግለት እንድቀጥል እያሳሰብን ድርጅታችንም ከቆራጡና ከታጋዩ የኢትዮጵያ ህዝብ ጎን በመሆን የሚፈለግበትን ሃገራዊ ግዴታ ለመወጣት ከመቸውም ግዜ በበለጠ እየሰራ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን።

አንፀባራቂ ድል ለኢትዮጵያ