ያንን ቄሮ ያንን ፋኖ

በርታ በሉት ያንን ቄሮ ያንን ፋኖ ጀግና

አይዞህ በሉት ከዚህ በላይ ምን አለና

ብሶት የወለደው

ደም ያንገፈገፈው

የጀግኖች ቃል ጥሪው

ወኔ የቀሠቀሠው

እነ ቄሮ አባ ፋኖው

የአያት ቅድመ አያት ቃል ኪዳን አደራ

ሰምቶ እንዳልሰማ ያልሆነ እናት ስትጣራ

የንጹሀን ደም መላሽ

ጠላት ገዳይ ጠላት ደምሳሽ

በርታ በሉት ያንን ቄሮ ያንን ፋኖ ጀግና

አይዞህ በሉት ከዚህ በላይ ምን አለና

የወገን አለኝታ ቀድሞ ደራሽ

የጭቁንን እንባ በደም አባሽ

ታሪክህ ተፅፏል በወርቅ ቀለም

ከትውልድ ወደ ትውልድ ይዘከራል ለዘላለም

በርታ በሉት ያንን ቄሮ ያንን ፋኖ ጀግና

አይዞህ በሉት ከዚህ በላይ ምን አለና

ቀስቅሳቸው ደቡቦችን ተጣራቸው የጋንቤላ መሰሎችን

የሶማሌ የአፋሩን ጭቁኖችን

የቤንሻንጉል ቆራጦችን

አሰልፈህ ከፍት ኋላ

የትግሉ ውል በጠላት እንዳይላላ

የነብርን ጅራት አይዙትም

ከያዙትም አይለቁትም

በርታ በሉት ያንን ቄሮ ያንን ፋኖ ጀግና

አይዞህ በሉት ከዚህ በላይ ምን አለና።

 

ከእውነቱ ቢወጣ