የነፃነት ትግል ጥሪ

በረዥሙ ታሪክህ በአስተዳደር ጥበብ፣ በጀግንነትህና በተፈጥሮ ሀብትህ የምትታወቀው ውድ የካፋ፣ ሸካ፣ ቤንች እና ማጂ ህዝብ ሆይ ምንም እንኳ ባለፉት ተከታታይ መንግስታት በደረሰብህ ግፍ፣ ጭፍጨፋ፣ ጫና እና በደል አንገትህ ደፍተህ ለመኖር ብትገደድም አሁን የግፍ ፅዋ ሞልቶ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ እህቶችህና ወንድሞችህ ጨቋኙን ሥርዓት ለማስወገድ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም መጪው ሥርዓት ላንተ እና ለልጆችህ የተሻለ ዕድል ይዞ ይመጣ ዘንድ ያንተ በትግሉ የጎላ ተሳትፎ ማድረግ ለነገ የማይባል ነው። ነፃነት፣ እኩልነትና ፍትሕ የሰፈነባት ሀገር ለመገንባት ዛሬውኑ ተነስ! ለሌሎች ወገኖችም አለኝታነትህን አስመስከር! በመላው ኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን ትግል ተቀላቀል! ነፃነትህን በራስህ ትግል ተቀዳጅ! እኩልነትህን በትግልህ አረጋግጥ! ፍትሕን በትግልህ አስፍን! ጭቆና በቃን! የሀብት ዘረፋን አንታገስም!  

ልጆችህ ትግሉን ለማስተባበር እየሠሩ ነው! ተነስ! ተዘጋጅ

ኖ ወራፎ ከፊነ ኖሚምዮና ሽገችነ!