ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨቱ የወያኔ ሤራ በከፋ፣ ቦንጋ ከሸፈ

በዓለማችን ላይ ለሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ኑሮ በአስፈላጊነታቸው ከታወቁ መሠረታዊ የምግብና መጠጥ ፍላጎቶች ባሻገር ማህበራዊ መስተጋብርን በመፍጠርና በማጠናከር አብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ህዝቦች ራሳቸውን ከድብርትና ከድካም የምያላቅቁበት ምናልባትም ትልልቅና ባለ ብርቱ ክንዳማ ሀብታም ሃገራትን አብላጫውን የሀብት ሚዛናቸውን በማጦዝ የሚታወቀው አረንጓዴ ወርቅ ቡና ስለመሆኑ ብዙዎችን የሚያስማማ ነው

ዘርና ሃይማኖት ሣይለይ የጾታ ልዩነት የእድሜ ገደብ ህግ ሣያግደው አብዛኛዎቹን የዓለም ህዝቦች የፍላጎት ማዕከል የሆነው በሃገራችን ደግሞ **የገቢ ምንጫችን ቡና ቡና የኢኮኖሚ ዋልታ ቡና ቡና ** የተባለውን የተፈጥሮ ፀጋ ሣትሣሣና ሳትነፍግ ያበረከተችው የኢትዮጵያዊቷ ምድር የካፋ አውራጃ ናት።

ኢትዮጵያ በዓለማችን አንዱ አድናቆት ያተረፈችው የሰው ልጅ መገኛነቷ በተጨማሪ የቡና መገኛ ምድር መሆኗ የዓለምን ትኩረት ያለምንም ማንገራገር የሳበ ትልቅ ጉዳይ ነው።

በቀድሞ ሥርዓቶች በነበረው አስተዳደራዊ መዋቅር በኢትዮጵያ 14 ክፍለ ሃገራት የነበሩ ሲሆኑ አንዱ የካፋ ከፍለሃገር ነው ። የካፋ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ጅማ ሆኖ በሥሩ 6 አውራጃዎች እንደነበሩትና ከ6ቱ አንዱ ካፋ ነች። በካፋ አውራጃ ሥር 10 ወረዳዎች መካከል የዴቻ ወረዳ ማኪራ ቀበሌ ደግሞ አረንጓዴ ወርቃችን የተገኘችበት ወርቃማ ምድር ነች።

ኮፊ(coffee) የሚለው ሥያሜ ካፋ ከተሰኘው የእንግሊዝኛው ሥርወ ቃል የመጣ ስለመሆኑ በርካታ የታርክ ጸሀፍዎች በድርሣናቶቻቸው ከትበውታል። ካፋ ከቡና መገኛነቷ ጋር በተያያዘ ቀደም ባሉት ዘመናት የዛይላና በርበራ ወደብን የንግድ መስመር ተከትሎ የበርካታ ዓረብ ሃገራት ነጋዴዎችን ከቀያቸው አርቆ ያተመማቸው ትልቅ የንግድ ማዕከል እንደነበረ የመካከለኛው ዘመን የታርክ ጸሀፊዎች ሳያቅማሙ ይስማሙበታል።

ካፋ የቡና መገኛነቱዋ ስለመሆንዋ እውነታውን በየጹህፎቻቸው ካስከመጡልን ከቢቤር ፣አምኖን ኦረንትና ሌሎችም የውጭ ጸሀፊዮች በተጨማሪ ከሃገራችን የታሪክ ምሁራን መካከል የእነ ፕሮፌሰር ላጲሶ ዴልቦ ሥራም የምጠቀስ ነው።

ከእነዚህና ከሌሎችም ታርካዊ እውነታዎች በመነሣት በ2000 ዓመተ ምህረት የተከበረውን ተኢትዮጵያ ሚኒሊየም በዓል ምክንያት በማድረግ እንደ ሃገር ከተሠሩት ትልልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ላይ የተገነባው ብሔራዊ የቡና ሙዚየም ኢትዮጵያ ከዛም ካፋ የቡና መገኛ ቦታ ስለመሆኗ ታሪካዊ እውቅና ስለመሆኑ የማያከራክር ሃቅ ነው።

ይሁን እንጅ በተለይም ወያኔ ኢትዮጵያን ማስተዳደር ከጀመረበት ካልፉት 26 ዓመታት ወዲህ ግን በከፋፍለህ ግዛ የብሔር ፖለቲካ መነሻነት ርካሽ የሆነ ያልተገባ የታሪክ ሺሚያ በማቆጥቆ ላይ ይገኛል።

እንደሚታወቀው ጅማ በቀደሞው አስተዳደራዊ መዋቅር የካፋ ክፍለ ሃገር ጠቅላይ ግዛት ወይም ዋና ከተማ እንድትሆን ሲወሰን ያለ አንዳች መነሻ አልነበረም፣ ከጊቤ ማዶ የሚገኘው አጠቃላይ ግዛት የካፋ ህዝብ አሠፋፈርን መሰረት ያደረገና ጅማም የካፋ ህዝብ መናገሻ ማዕከል ከማድረጉም ባለፈ ጅማና የካፋ ህዝብ የ አንድ ሣንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለመሆናቸው ተፈጥሮ በራሷ እውነተኛ ምሥክር ነች።

በመሁኑም በወያኔ አገዛዝ ሥርዓት ወቅት የኦሮሚያ ህዝብና ክልል መንግስትን የማይውክሉ እንዲሁም የሁለት ህዝቦች የብዙ መቶ ዓመታት ወዳጅነትና ዝምድና መተሳሰብ ብሎም በተለያዩ ሁኔታዎች በትስስር መኖራቸው ያሳሰባቸው የወያኔ ካድሬዎች በወጠኑት ሴራ ቡና የተገኘው ካፋ አዎራጃ ማኪራ ቀበሌ ሣይሆን ጅማ ዞን ነው እየተባለ የሚናፈሠው የተዛባ መሠረተ ቢስ ታርክ በእጅጉ አሳዝኖናል።

ቡና ካፋ በመገኘቱ አጠቃላይ እውቅናው የኢትዮጵያ እንጅ የካፋ አለመሆኑ በግልፅ እየታወቀ ግን ደግሞ ታሪክን በእውነትነቱ ከመቀበል በአፈንጋጭነት ዝንባሌ በፀብ አጫሪውች ግፊት ወደ አልተፈለገ ድምዳሜ መድረሱ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው።

በኦሮሞ ህዝብና ክልል ሥም የሚነግዱ የወያኔ ካድሬዎች ድብቅ አጀንዳና መፈክር ጎላ ብሎ መስተጋባት የጀመረው በተለይም የቡና ሙዚየሙ እንዲገነባ በፌደራል መንግስት ከተወሰነበት ግዜ ጀምሮ ሲሆን አሁን በቅርቡ ከታህሣሥ 7 ጀምሮ 3 ቀናት የፌደራል መንግስት ባዘጋጀው የቡና አፈላል ሲምፖዚየም ላይ ከቡና መገኛነት ጋር ተያይዞ የተዘጋጀው ፓናል ውይይት ከኦሮሚያ መጡ በተባሉ ተወካዮች እንቢተኝነት ሣይካሄድ መቅረቱ ይህ የተዛባ እውነታና የወያኔ መንግስት ግጭት የመፍጠር ዝንባሌ ፍላጎት የቱን ያክል ወደ አበቃለት የአስተሳሰብና የአመለካከት ብልሽት ጫፍ ስለመድረሱ ማሣያ ነው።

የዚህ ጹህፍ አዘጋጅ አመለካከትና እምነት ከሆነ በተሣሣተ ፍላጎትና ግፊት በመነሣሣት ለበርካታ ዘመናት በአብሮነት የኖረውን ህዝብ ከማጋጨት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ በቅጡ እንድረዳው እያሳሰብን ምን አልባትም የግጭት ፈላጊ ኃይሎች አጀንዳ ከማራገብ አኳያ አውቀውም ይሁን ሣያውቁት የዚህ አስተሣሰብ ሠለባ የሆነ መንአልባትም የኦሮሞን ህዝብና የክለሉን መንግስት ሣይሆን የግል አመለካከታቸውን የሚያራምዱ ኃይሎች ከዚህ ድርግታቸው እንድቆጠቡ ሌላው መልዕክታችን ነው።

የካፋ ዞን( የቀድሞ የካፋ አውራጃም) ቢሆን የቡናን ጥራት ሣያስጠብቁ ቡና አብቃይ በሆነችው ብርቅዬ ምድር የሚኖረው ህዝብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም በአግባቡ ሣያረጋግጡ ብሎም የራሱን አቅምና ሃብት አስተባብሮ የአረንጓዴ ወርቁን ተፈጥሮአዊ ጣዕም ለማጣጣም የተመሠረተውን የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዬን እንኳን ከረጃጅም ሌባ እጆች መታደግ ሣይችል የቡና መገኛ ነኝ ማለት ብቻውን የትም አያደርስም።

ስለሆነም ከብዙ ዘራፊዎች ማለትም ከነብርሃኑ አዴሎና ታምሩ ታደሠ የዝርፊያና የምዝበራ መዕከል በትንሹም ቢሆን ተርፎ በመንገታገት ላይ የሚገኘውን ዩኒዬን በዘመናዊ መልኩ በማደራጀት ዓለም ዐቀፍ ተሞክሮ እንድቀስምና ራሱን አጠናክሮ ከዘርፉ  ከሚገኘው ጥቅም ተቋዳሽ እንዲሆን ማድረግ።

በአርሶ አደሩ መንደር ከቡና ተክል እስከ ለቀማ በግንዛቤ እና በእውቀት እጥረት የሚስተዋለዎን የቡና አያያዝ መሠረታዊ ችግሮች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመቅረፍ የአርሶ አደሩ ህይወት ከቡና ግብይት በሚገኘው ገቢ እንዲለውጥ ማድረግ።

የካፋን ቡና ተፈጥሮአዊ ጣዕምን የሚያውቁና የተለየ ግምት ያላቸው እንዲሁም የካፋን ቡናን በዓለም ገበያ በማቅረብ ረገድ ተሞክሮ ካላቸው የአውሮፓውን በተለይም የጀርመን ባለሃብቶች ጋር ኢኮኖሚያዊ ቁርኝነት በመፍጠር ወደ ውጭ ገበያ የሚላከው ቡና በመጠንና በጥራት ከፍ እንድል ማድረግ የዘርፍን ጥቅም ያሣድጋል።

ሌላውና ሊታለፍ የምይገባው ጉዳይ የዞኑ አብዛኛው መሬት ለቡና ማብቀል የተስማማ በመሆኑ መሬት በባንክ እያስያዙ ለሚኮበልሉና ደን እየጨፈጨፉ ዞኑን እርቃኑን አስቀርተው የራሳቸውን ሃብት ለሚያካብቱ ባለሃብቶች ነን ለሚሉ የጠራራ ፀሃይ ዘራፊዎች ጋር እየተባበሩ የዞኑን ህዝብ የበይ ተመልካች ከማድረግ እና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ አርሶ አደሮችና ወጣቶችን በማስተባበር እውነትም ካፋ የቡና መገኛ የሚለውን ታርክ በድጋሚ በወርቃማ ቀለም አድምቆ ማደሱ ተገቢ ነው እንላለን።