መቋጫ ያልተገኘለት የሸካ ህዝብ የዘመናት ውስብስብ ችግር መፍትሔው ማን እጅ ነው ያለው? 

በሐገራችን በተለያዩ ወቅቶች በተፈራረቁ ሥርዓቶች የተለያዩ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እና ሥያሜዎች ሥትጠራ የቆየችው የቀድሞዎ የሞቻ አውራጃ አሁን ባለው ሥርዓት ደግሞ በደቡብ ክልል ሥር ከሚገኙ ዞኖች አንዷየሆነችው የሸካ ዞን ተፈጥሮ የቸራት ውብና ድንቅ ምድር በውስጧበርካታ ብሔር ብሔረሰቦችን አቅፍ ትገኛለች:: 

የሸካ ዞን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ካሉት ዞኖች በጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደን ባለቤትነቷ ከመታወቛም ባሻገር የተፈጥሮ ቡና አብቃይና በማርና ቅመማ ቅመም ምርቶቿ የበርካቶችን ቀልብ የሳበች የታታርና የእንግዳ ተቀባይነቱ እንድሁም በጅግንነቱ የምታወቅ ህዝብ መገኛ ለምለም ምድር ስለመሆኑዋ ዛሬም በታርክ ጸሃፊዎችና ነዋርዎች አንደበት በአድናቆት ትዘከራለች።

በሸካ ምድር የምገኙት ሸከቾች ብቻ ሳይሆኑ መዠንንግር፣ ሸኮ፣ ካፋ፣ ቤንች፣ ኦሮሞ፣ እና ሌሎችም ህዝቦች በመፈቃቀድ በመፈቃቀርና በመተሳሰብ እንደ አንድ ህዝብ ሆነው ይኖራሉ። 

እነዚህ ህዝቦች በሰላምና በመከባበር ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን በረከት እየተጋሩ የሚኖሩ ሲሆን ባለፉት ሥርዓቶች በሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተቃራኒ የሚነሱ ኢፍትሀዊ አሰራሮችን በመቃወም ለመብቶቻቸው መከበርና ለዘላቂ ጥቅማቸው መረጋገጥ የህይወት መስዕዋትነትን እስከመክፈል የደረሰ የጀግንነት ታርካቸው አሁን እስካለው ትውልድ ለውደፊትም እስከሚመጣው በዘመን ተሻጋርነት ሲወሳና ሲዘከር ይኖራል።

ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሀብት የበለጸገችው የሸካ ዞን ፈጣሪ በኪነ ጥበቡ ውብና ድንቅ አድርጎ የፈጠራት ብትሆንም ካለፉት ሥርዓቶች እስከዛሬ ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች በተለየ ሁኔታ ከመልካም አስተዳደርና ከፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል አንጻር በእጅጉ የተበደለችና የተረሳች ምድር ነች።

እንደው ከቅርብ ጊዜ ታሪክ ማለትም የወያኔ መንግስት ሃገርቱን አስተዳድራለሁ ብሎ የ አፈናና የጭቆና ሥርዓቱን ካሰፈነበት ግዜ ጀምሮ በዚህ ኩሩና ታታሪ በሆነው ህዝብ ላይ በዓይነቱ አሣዛኝና ዘግናኝ ድርጊት እየተፈጸመ ሥለመሆኑ ምንም ማጣቀሻ ሳያስፈልግ ወይንም ማስረጃ መዘርዘር ሣያሻ መሬት ላይ ያለው እውነታ በዳይ የሆነውን ሥርዓትና ተበዳዩን ህዝብ የሚያግባባ እውነታ ስለመሆኑ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ሊጠቁም ይወዳል።

የኸው ሃገርቱን እየገዛ ያለው አፋኝና ጨቛኝ ሥርዓት የፈጠራቸውና ከህዝቡ አብራክ የተገኙ ህሊና የጎደላቸው ሆዳቸው አምላካቸው የሆኑ ታማኝ የወያኔ ሎሌዎች አባሪ ተባባሪ በመሆኑ እየፈጸሙት ያለው ልክ ያጣ ግፍና በደል ሌላኛው የሸካ ህዝብ ሰቆቃ ነው።

ዞኑን ያስተዳድሩ ተብለው በተለያዩ ወቅቶች የተሾሙ የዞኑ ተወላጆች ነን የሚሉ የወያኔ ታማኝ አገልጋዮች አቶ ወዶ አጦ እና አቶ በፍቃዱ ድሉ የተባሉት በአስተዳደር ዘመናቸው ከፈጸሟቸው ታሪካዊ ሥህተቶችና በህዝቡ ላይ ካደረሷቸው በደሎች በጥቅቱ ለመግለጽ ያክል፣

1 ፥ በኢንቨስትመንት ሥም ከወያኔ ባለሥልጣናት ጋር በሽርክና እና በተባባሪነት ለሚንቀሳቀሰው ሼክ መሀመድ ዓላሙዲን ከ 10 ሺ ሄክታር መሬት በላይ ገማድሮ አካባቢ ለቡና ተክል የሚሆን መሬት በርካታ አርሶ አደሮች እንዲፈናቀሉ ተደርጎ ተሰጥቷል።

የሚገርመው ለጥቂት ወያኔ ባለሥልጣናት ወኪል ሆኖ የዞኑን እጭቅ የተፈጥሮ ሀብት እንድበዘብዝ እና እንዲዘርፍ ፈቃድ የተሰጣቸው ሼክ መሀመድ ዓላሙዲን በለመደው የዘረፋና የሽንገላ ሥልቱ ለዞኑና ለአከባቢው ህዝብ ሆስፒታልና ለሎችንም መሰረተ ልማቶች እዘረጋለሁ ብሎ የማለውን ማሀላ እና የገባውን ቃል ኪዳን ከላይ ሥማቸው የተገለጹት ተላላኪ አስተዳዳሪዎች ነን ባዮች በራሳቸው ጥቅም በእጃዙር ኪሳቸውን በጉቦ በማደለብ የዞኑን ህዝብ ሂሳብ አወራርደዋል።

2፥ ሌላው ኢስት አፍርካ ለተባለው ድርጅት በተመሳሳይ በርካታ አርሶ አደሮችና ቤተሰቦቻቸው ከመረታቸው ቴናቅለው የሻይ ተክል ማምረቻ እንድሰጣቸው በመደረጉ ዛሬ እነ አቶ በፍቃዱ ዲሎ አዲስ አበባ ላይ በተንጣለለ እና ውድ በሆነ ዋጋ በተገዛ እቤት እንዲኖሩ መደረጉ አሳዛኝ እና ልብ የሚሰብር አስነዋሪ ድርጊት ነው።

3፥ በእነ በፍቃዱ ዲሎ አስከፊ ድርጊት በዚህ ሳያበቃ በትንደላቀቀ ኑሮ ለሚኖሩና ለህዝብ ደንታ ለሌላቸው ለእነ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ለበላይ ወላሻ እንዲሁም ለሚሊዮን ወልዴ በኢንቨስትመንት ሥም የዞኑ ህዝብ የተጎሳቆለ ህይወቱን የሚመራበትን መሬት በመንጠቅ በራሳቸው የጥቅም ሥሌት አሳልፈው በመስጠት ህዝቡን የበይ ተመልካች በማድረግ ለረሃብና ለእርዛት የመደረጋቸው ምሥጥር ባለቤቷን ያመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች´´በሚለው የአበው ተረት ይደመደማል።

አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ታዋቂነቱን በመጠቀም ግን ደግሞ ጥቂት ሆዳም እና ህሊናቸውን ለጥቅም አሳልፈው ከሰጡ ዘራፊና ወንበዴ ከሆኑ የዎያኔ ባለሥልጣናት ጋር በመደራጀት በብዙ ሺዎች የሚቆጠር ሄክታር መሬት ለኢንቨስትመንት ሲሰጠው እሱም ልክ እንደ ሼክ ዓላሙዲን ለአከባቢው ህዝብ የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን እዘረጋለሁ ብሎ ምሎ ተገዝቶ ጥቅሙን ቢያስከብርም እንኳን ይህንን ሊያደርግ ይቅርና በድርጅቱ ላይ ተቀጥረው ለሚሰሩ  ምንደኛ ህጻናት ሊከፈል የሚገባውን የወዛደርነት እራፊ ሣንቲም በአግባቡ እየከፈለ አለመሆኑ ሲታይ የበደሉን እና የግፍን መጠን በእጅጉ ያጎለዋል።

በፍቃዱ ዲሎ በአስተደኣደር ዘመኑ ከፈጸማቸው እነዚ ታርካዊ በደሎችና የግፍ አስተዳደር አኳያ በተለያየ መንገድ በዞኑ ህዝብ ጥቅም ላይ ተደራድሮ ያካበተው ሃብት እንዲያጣትም በሥመ ግምገማ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ ሄዶ በተገዛለት እቤትና በእነ አትሌት ኃይሌ እና በመሰሎቹ በሌላ ሰው ሥም የተከፈተለትን የ፭ሚሊዬን ብር ሂሳብ እየመነዘረ የተደላደለ ኑሮ እንዲኖር ሲደረግ መቸም ታማኝ እና ለዞኑ ህዝብ ጥቅም የሚቆረቆሩ ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸው እነ አዝመራው ያሉበት ሥብስብ ዞኑን ተረክቦ የማስተዳደር እድል አግኝቷል።

ይሁን እንጂ በአቶ አዝመራው አስተዳዳርነት የሚመራው የካቢኔ አባላት በእነ ፍቃዱ ዲሎ የተፈጸመውን ግፍና በደል በማጣራት ለክልሉ ፀረ ሙሲና ኮሙሽን ዝርዝር መረጃ በማቅረቡ የተነሳ የእነ ፍቃዱና የግብረ አበሮቹ የዘራፊ ባለሃብቶች ኃይል በፈጠረው ተፅዕኖ በተገላቢጦሽ የተራማጅ አስተሳሰብ ባለቤቶች ስብስብ በአጭር ግዜ ውስጥ የተለያየ ታርጋ ተሰጥቶአቸው ወደ ማረሚያ እንዲወርዱ መደረጉ ሁኔታውን ተስፋ አስቆራጭ ደረጃ ላይ እንዲደርስ አድርጎታል።

እነዚህንና ሌሎችንም አስተዳደራዊ በደሎችን ሲፈፅም የቆየው በፍቃዱ ዴሎ እና ከእርሱ ጀርባ ሆነው የዞኑን ህዝብ ደም የሚመጡ የዎያኔ ባለሥልጣናት እና የተደራጁ ዘራፊ ባለሃብቶች ሁኔታ የክልል መንግስት ነኝ እያለ ራሱን በሚጠራው በደቡብ ክልል መስተዳድር ቁልጭ ብሎ እየታወቀ አንዳችም ዓይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ዛሬም የበፍቃዱን ፍላጎት የሚያሟሉና ጉዳይ የሚያስፈፅሙ የዞኑ አስተዳደርና ካቢኔዎች በዞኑ ህዝብ ላይ የሚደርሰውን ግፍና በደል የተደራረበ እና ማቆሚያ የሌለው እንዲሆን በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ የጠጠር መንገድ ለሼካ ዞን ህዝብ የቅንጦት ጉዳይ ሆኖ የህልም እንጀራ በመሆኑ የበርካታ እናቶች ህይወት በወሊድ ምክንያት እየተቀጠፈ ይገኛል። ያ ኩሩና ታማኝ እንዲሁም ከልክ ባለፈ ሁኔታ በትዕግስተኝነት የሚታወቀው ህዝብ ንጹህ የመጠጥ ውሃ እንዲያገኝ ባለመደረጉ ቁጥራቸው ጥቂት የማይባሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ንፅህናው ያልተጠበቀ ውሃ በመጠጣት በተለያየ ህመም እና ብሶታቸውና በደላቸው እስከ ወዲያኛው  በሞት እየተሰናበቱ መሆናቸው ሲታይ የዚህ ዓይነቱ ግፍና በደል ማቆሚያው የት ይሆን መፍትሔውስ በማን እጅ ነው ብሎ መጠየቅ ግድ ያለበት ግዜ ላይ ደርሰናል።

ውድ አንባቢያን ከላይ የተዘረዘሩት  ችግሮችና የዞኑ ህዝብ እየተጋፈጣቸው ያሉ በደሎችን ለማስቀረት የተከበረው የሸካ ዞን ህዝብ ዛሬም ልክ እንደ ትናንቱ በገነፈለ የወትሮ የጀግንነት ወኔ እና አልደፈር ባይነት አካኪ ዘራፍ ብሎ ጫካ መግባት ጦር በመማዘዝ የተነጠቀውን መብት ማስመለስ ጥቅሞቹን ማስከበር ጠፍቶት ሳይሆን ከዛሬ ነገ ይሻላል በግል ጥቅም ዓይናቸው የታወሩ ግፈኞች ወደልቦናቸው ይመለሳሉ፣ ግድ የለሹ የወያኔ ሥርዓትም ምን አልባት ከረፈደም ቢሆን የዘገየ ፍትህ ይሰጠኝ እንደሆን ብሎ በተለመደው አስትዋይነቱ በትዕግስት በመጠባበቅ ላይ ቢገኝም ሁሉም በየፊናው አሻፈረኝ ብሎ በእኩይ ድርጊቱ ቀጥሎበታል።

እናም የዚህ ጽሁፍ አቅራቢና ሌሎችም መላው ተራማጅ አስተሳሰብ ያላቸው አካላት እንደሚያምኑት በኢትዮጵያ አሁን ያለው የወያኔ አገዛዝ በህዝቡ ላይ እያደረሠ ያለው የግፍ አገዛዝ እንዲያቆምና መፍትሔ እንዲበጂለት ሁሉም በያለበት ድምጹን በማሰማት ላይ ይገኛል።

ስለሆነም እንኳን በሸካ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጭቆናና በደል በቅርጹም በይዘቱም በጥልቀቱም ከሌላው ጋር ሲነጻጸር ጠንከር ያለ ቢሆንም ይህም የሥርዓቱ ብልሽት ድምር ውጤት በመሆኑ ከሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ጥሰት አንድ የሚያደርጉ መሠረታዊ ምክንያቶች አኳያ ሁሉም ያገባኛል ባይ በያለበት ድምጹን ከፍ አደርጎ የሚያሰማበት ትክክለኛ ግዜው አሁን ነው።

የሸካ ህዝብ ከኖረበት ከልክ ያለፈ ትዕግስት አዘቅት ውስጥ በመውጣት በተለያዩ ወደ መፍትሔ አቅጣጫ ሊያደርሱ የሚችሉ የትግል አማራጮችን በጠንካራ የአልበገር ባይነት ሥሜት ዝምታውን በመስበር የተጠማውን ፍትሕ የተነፈገውን መብት ያስከብር ዘንድ የችግሩ ሰለባ እንደሆነ ሁሉ መፍትሔውም በእጁ ነው እላለሁ። በሌላ ግዜ በተመሳሳይ እና ወቅታዊ መረጃዎች እስከምንገናኝ የሸካ ህዝብ መብት ለማስከበር ዛሬም ወሳኝ ቀን ነው አልረፈደም በማለት የምሰናበታችሁ እውነቱ አይቀርም ነኝ

ቸር እንሰንብት።

moderator@kaffamedia.com